All Of Me For All Of You - Amharic CD Cover

እናመልክሃለን 

ከዶር. ኖኤል ውድሮፍ እና ከኮንግረስ ሙዚቃ-ፋብሪካ የቀረቡትን እነዚህን ጸሎቶች እና የአምልኮ ዝማሬዎች ከእናንተ ጋር ለመካፈል በመቻላችን ደስታ ይሰማናል። “እናመልክሃለን” የሚለው አልበም የእኛን የጋራ አምልኮ ልብ እና እንዲሁም ለእግዚአብሔር ያለንን አክብሮት እና ምስጋና ያንጸባርቃል። 

በዚህ አልበም ላይ የተሳተፉት መዘምራኖች፥ ኳየሮች፥ ግጥም-ጸሐፊዎች እና ሙዚቀኞች፥ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አካል ውበቱን በእውነት አንጸባርቀውታል። እነዚህም ተሳታፊዎች የመጡት ከተለያየ የምድር ዳርቻ የምድር ዳርቻ ነው - ማለትም ከካሪቢያን፥ ከዩናይትድ-ስቴትስ፥ ከአውሮፓ፥ ከአፍሪካ፥ ከኤዥያ፥ ከላቲን-አሜሪካ እና ከፓስፊክ አገሮች - አሁን በአለም ዙሪያ ከሚገኙት ቤተክርስቲያኖቻችን እና አማኞች ጋር እየተካፈልን ያለነውን ይህንን ሰማያዊ አቅራቦት ለመፍጠርና ለመተባበር የመጡ ናቸው።