እናገንሃለን

እናገንሃለን’ አልበም ከዶር ውድሮፍ እና ከኮንግረስ የሙዚቃ-ፋክተሪ በቅርቡ የተውጣጡትን የጸሎቶች፣ የመዝሙሮች እና የአምልኮ ቅንብሮች ያቀፈ አልበም ነው።

ይህ ኃይለኛ የአምልኮ አገላለጽ የሚፈስሰው፥ የእግዚአብሔርን ግርማ፥ ሉአላዊነቱን እና ክብሩን በማክበር እና የእርሱን እሴቶች፣ ባሕርያቱን እና ማንነቱን በምድር ላይ በመግለጽ ላይ ከሚገኘው አለም-አቀፋዊ ህዝብ አመስጋኝ ልብ ውስጥ የወጣ ነው።

ይህ አልበም በጋራ ጉዞአችን ውስጥ ወሳኝ የሆነውን ክስተት የሚወክል ነው። በእንግሊዝኛ-ቋንቋ የተሰራው አልበም የተቀዳው፥ የኮንግረስ የፈጠራ ማዕከል በሆነው በኤላጃ ሴንተር ውስጥ በተደረገው ልዩ የቅጂ ክፍለጊዜ ላይ ነው። ይህ ክፍለጊዜ የተካሄደው በዶር ውድሮፍ እና በባለቤቱ በሲስተር ጁን አማካኝነት ሲሆን፣ እንዲሁም የኤላጃ ሴንተር ቅዱሳኖች እና ከትሪኒዳድ-ቶቤጐ የመንግሥቱ ማህበረሰብ ኔትወርክ ከተመረጡት ተወካዮች ጋር አንድላይ በመሆን በዚህ የቅጂ ክፍለጊዜ ላይ ተሳትፈዋል።

ከዚያም በአለማችን ዙሪያ የሚገኙት ዘማሪዎች እና ሙዚቀኞች፥ ይህንን የአምልኮ አቅራቦት ከ14 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ለመስራት በአንድላይ ይገናኛሉ። ስለዚህ አሁን፥ ከምድር ዙሪያ ሁሉ ውብ የሆነ የምስጋና እና የአምልኮ ድምጽ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የሚያቀርብ የቅዱሳኖች ድምጽ መሰማት ይችላል።